ጠ/ሚኒስትር አብይ ከሐምሌ 25 -2017 ዓ.ም አቶ አዲሱ አረጋን በዶ/ር ግርማ አመንቴ ምትክ የግብርና ሚንስትር አድርገው መሾማቸውን ተከትሎ ለጉዳዩ ቅርብ በሆኑ ምንጮች ተሰናባቹ ሚንስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ የዲፕሎማቲክ ተልእኮ ይሰጣቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያስነበበው ፎርቹን ነው፡፡
ከፎርቹን ዘገባ መመልከት አንደቻለው አቶ አዲሱ አረጋ ባለፉት አመታት በክልል ደረጃ የሰሩበት መሰረታዊ የገጠር ልማት ስራ እና ለገዥው ብልፅግና ያላቸው ቅርበት በግብርና ሚንስቴር ሹመታቸው በምግብ ዋስትና እንደዚሁም በማክሮ ኢኮኖሚክ ማረጋጋት ላይ በፖሊሲ ትኩረታቸው ቀዳሚ ስፍራ ሊይዙ እንደሚችሉ አመላክቷል፡፡
ነገር ግን የአቶ አዲሱ አረጋ ሹመት በአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ዘንድ በአይነ ቀራኛ የሚታይ ነው ሲል የገለጸው ዘገባው ምክንያት ያለውንና የአዲሱ የሚኒስትር የቤት ስራዎች ያላቸውንም አስፍሯል፡፡
