አከራካሪ የነበረው ግብር የማይከፈልበት የደመወዝ መጠን ማሻሻያ ሳይደረግበት 2 ሺሕ ብር ሆኖ ጸደቀ

Date:



600 ብር የነበረው ግብር የማይከፈልበት ከደመወዝ የሚገኝ ገቢ እንዲሻሻል ጥያቄ እየቀረበበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴርም ሥራ ላይ ከዋለ 9 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የገቢ ግብር አዋጅ እንዲሻሻል ረቂቁን አዘጋጅቶ ሊሚኒስቴሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም በረቂቁ ላይ ከተወያየበት በሗላ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኮታል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ከተካተቱ አከራካሪ ጉዳዮች መካከል ከግብር ነጻ የሚደረገው ከደመወዝ የሚገኝ ገቢ 2 ሺሕ ብር እንዲሆን የሚደነግገው አንቀጽ አንዱ ነው፡፡

ድንጋጌው በረቂቅ አዋጁ ላይ በተካሄደ ውይይት ወቅት የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከበርካታ ሰዎች ተቃውሞ ቢገጥመውም፤ በዛሬው ዕለት ማሻሻያ ሳይደረግበት 2 ሺሕ ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

በአዋጁ አንዳንድ ድንጋጌዎች እንዲሻሻሉ ሐሳብ ከሰጡ የምክር ቤት አባላት መካከል ደሣለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ይገኙበታል፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ “አዋጁ የሰራተኞችን የኑሮ ጫና ያላገናዘበ ነው” የሚል ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም “ከድህነት ወለል በታች ካለ አንድ ሠራተኛ ግብር መሰብሰብ ሰብዓዊነት እና ርህራሄ የጎደለው አዋጅ ነው” ብለዋል፡፡

የገቢ ግብር ማሻሻያ አንዱ ዓላማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያለባቸውን የግብር ጫና መቀነስ እንደሆነ በረቂቁ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ በክልልና በታችኛው የመንግሥት መዋቅር ባሉ አስተዳደሮች ከፍተኛ ገቢያቸው ከደመወዝ የሚያገኙት ግብር በመሆኑ መነሻው ከፍ ባለ ቁጥር ገቢያቸው እንደሚያሽቆለቁል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስር ድኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ለኅብረተሰቡ የሚቀርበውን አገልግሎትም አደጋ ውስጥ ይከተዋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም በክልሎች የሚገኘውን ገቢ እንዳያሳጣ ተብሎ መዘጋጀቱን ተገልጿል፡፡

ይህንን በሚመለከት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ የቋሚ ኮሚቲው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ምላሽ ሲሰጡ እንደገለፁት፤ “2 ሺሕ ብር የሚለው መንግሥት ማግኘት የነበረበትን 38 ቢሊዮን ብር እንዲያጣው ተድርጎ ነው” ብለዋል፡፡

ሌላው ጥያቄ የተነሳበት የአዋጁ ክፍል “ዓመታዊ የገቢ ግብር አሰባሰብ በሩብ ዓመት እንዲሆን መቅረቡ መጨናነቅን ከመፍጠርም በላይ በዓመቱ መጨረሻ ሊከስር ይላል” የሚሉት የምክር ቤት አባሉ ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ፤ ይህ መስተካል አለበት የሚል ጥያቄም አንስተዋል፡፡

ይህንን በሚመለከት ከገንዘብ ሚኒስትር እና ከቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡

በሩብ ዓመት መሆኑ ታክስ አስተዳደር ስርዓቱን የሚያስተካልና የነጋዴውንም ጫና የሚያቀል መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“ይህ አዋጅ በጀት ሲጸድቅ የጸደቀ ነው” የተባለ ሲሆን፤ የገቢ ማሰባበቢያውን ማሳካት የሚያስፈልግ በመሆኑ ከሀምሌ ጀምሮ ወደ ስራ እንደገባ ለማስቻል የታሰበ መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ተብሏል።

ይህ አዋጅ ከሰሞኑም ውይይቶች የተደረጉበት ቢሆንም ጥያቄ ያስነሱት ከግብር ነፃ የሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የመሰሉ ጉዳዮች ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግባቸው አዋጁ በስድስት ተቃውሞ በ12 ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...