አየር መንገዱ ለ2500 አባወራዎች መኖሪያ ቤቶች እየገነባ ነው

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚያስገነባው ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 2,500 አባወራዎች እንደሚነሱ መገለጹ ይታወሳል።

3,500 ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፈው አዲሱ የአየር ማረፊያ ግንባታ፣ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ  ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ በአሁኑ ሰአት ለ2,500 አባወራዎች መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንና በመስከረም ወር ለማስረከብ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

“አካባቢው ላይ የነበሩ ገበሬዎች ተነስተው የሚሰፍሩበት ቦታ ግንባታ በሰፊው እየተከናወነ ነው፤ መስከረም ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው፤ እንደተጠናቀቀ ወደ ተሰራላቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ይዘዋወራሉ፡፡” ብለዋል፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...