አዲስ አበባ የ2026 የዓለም የብስክሌት ኤሊሚኔተር መክፈቻ አስተናጋጅ ሆናለች

Date:

የ2026 የዓለም የብስክሌት ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ የመክፈቻ ውድድር መጋቢት 20, 2018 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ይህ ውድድር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ የከተማ ውስጥ የብስክሌት ውድድር ይሆናል ተብሏል።

በውድድሩ ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል ተወዳዳሪዎች በሁለቱም ጾታ ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የዚህ ውድድር አዘጋጅ መቀመጫውን ቤልጂየም ያደረገው ሲቲ ማውንቴን ባይክ (City Mountainbike) ነው

ውድድሩ ምን አንነት መልክ አለው ?

ኤሊሚኔተር (XCE) የተባለው ይህ የብስክሌት ውድድር ዘርፍ፣ ተወዳዳሪዎች በከተማ መሃል በተዘጋጁ አጫጭርና ሰው ሰራሽ መሰናክሎች በሚገኙባቸው መንገዶች ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የሚፎካከሩበት ነው።

በአንድ ጊዜ 4 ተወዳዳሪዎች አብረው የሚለቀቁ ሲሆን ውድድሩ በጣም አጭርና ፈጣን ነው።

መጀመሪያ የደረሱት ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ፤ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ግን ከውድድሩ ይሰናበታሉ። ይህ ሂደት አንድ አሸናፊ እስኪቀር ድረስ ይቀጥላል።

የአዲስ አበባው ውድድር እንደተጠናቀቀ የውድድር ዘመኑ ቀጣይ ዙር በታጂኪስታን ዱሻንቤ ከተማ የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...