የቤልጂየም ፍርድ ቤት በፓትሪስ ሉሙምባ ግድያ ዳግም ምርመራውን ከፈተ

Date:

የኮንጎዉ የነፃነት ታጋይ ተምሳሌት የፓትሪስ ሉሙምባ ቤተሰቦች ፍትህ ለማግኘት ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የቤልጂየም ፍርድ ቤት በ1961 የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ብቸኛው በህይወት ያለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

የሉሙምባ ዘመዶች በግድያው ላይ የቤልጂየም ባለስልጣናት ረጅም ጊዜ የዘገየ የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር ስለነበራቸው ተባባሪነት ላለፉት 15 ዓመታት ሲወተውቱ ቆይተዋል።

የሟቹ የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር የልጅ ልጅ የማ ሉሙምባ በብራስልስ ፍርድ ቤት በዝግ ከሚካሄደው ችሎት በፊት ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል‹‹ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ አንችልም፤ነገር ግን የቤልጂየም የፍትህ ስርዓት ስራውን እንዲሰራና እውነታውን ይፋ እንደሚያደርግ ተስፋ እናደርጋለን››ብለዋል።

ሉሙምባ በቀድሞዋ ቅኝ ገዢ ቤልጂየም ቅጥረኛ ወታደሮች እርዳታ ተረሽኖና አስከሬኑ በአሲድ እንዲሟሟ ከተደረገ ከ65 ዓመታት በኋላ፤ ለፍርድ የሚቀርብ አንድ የቀድሞ ባለስልጣን ብቻ በህይወት ይገኛል።

እርሳቸውም የ93 ዓመቱ ኤቲየን ዳቪኞን ሲሆኑ፤ አንድ ወቅት የአውሮፓ ኮሚሽነር የነበሩና ሉሙምባ በተገደለበት ወቅት ጀማሪ የቤልጂየም ዲፕሎማት ነበሩ።

ግለሰቡ በቤልጄም ፌዴራል አቃቤ ህግ በሉሙምባ ህገ-ወጥ እስራትና ዝውውር እንዲሁም አዋራጅና ዝቅ የሚያደርግ አያያዝ በመፈጸም ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ተከስሰዋል።

ዳቪኞን የቤልጄም ባለስልጣናት በግድያው ውስጥ ተሳትፎ እንደሌላቸው ሁልጊዜም የሚክዱ ሲሆን፤ ጠበቃቸውም  ከዝግ ችሎቱ በፊት ለኤኤፍፒ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...