ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ሊያልፍ የነበረ ነዳጅ ጫኝ መርከብ መምታቷን አስታወቀች

Date:

አብዮታዊ ዘቡ በቴሌግራም ቻናሉ ባወጣው መረጃ፤ “ፕሪማ” የሚል ስያሜ ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከብ በወሽመጡ በኩል “መተላለፍ እንደማይቻል” በባሕር ኃይሉ የተሰጠውን “ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ችላ በማለቱ በድሮን መመታቱን ገልጿል።

“ከጠበኛ አገራት ጋር አጋር የሆኑ” ነዳጅ ጫኝ እና የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፍ እንደማይፈቀድላቸውም ወታደራዊ ኃይሉ አስገንዝቧል።

በዓለም ላይ ካሉ ወሳኝ የኃይል ማጓጓዣ መስመሮች አንዱ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ፤ ከዓለም አቀፉ የነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦት አንድ አምስተኛ የሚሆነው ይተላልፍበታል።

በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የመርከብ መተላለፊያ መስመሩ ሙሉ እንዲቆም አድርጎታል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የኢራን መንግሥት በመስመሩ ለመተላለፉ የሚሞክሩ መርከቦችን “በእሳት እንደሚያያይዝ” ዝቷል።

ኢራን ይህንን ካለች በኋላ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “አስፈላጊ ከሆነ” የአሜሪካ ባሕር ኃይል በዚያ የሚያልፉ መርከቦችን እንደሚያጅብ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...