ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

Date:



ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ድርድር የምትቀበለው “ፍትሃዊ እና ሁሉን አቀፍ ስምምነትን” ብቻ እንደሆነ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልፀዋል::

ይህ የተባለው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሂደቱ ላይ “ትልቅ መሻሻል” መኖሩን በጠቀሱበት ወቅት ነው።

“በድርድሩ ወቅት ህጋዊ መብቶቻችንን እና ጥቅሞቻችንን ለማስጠበቅ የተቻለንን እናደርጋለን” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ በቤጂንግ ከቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዩ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ መናገራቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

“እኛ የምንቀበለው ፍትሃዊ እና ሁሉን አቀፍ ስምምነትን ብቻ ነው “ ያሉት ሚንስትሩ፥ ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረገውን የአሜሪካ መርከቦች አጃቢ እንቅስቃሴ ለማቆም ያቀረቡትን ሀሳብ በቀጥታ አልጠቀሱም።

ይህ የትራምፕ እርምጃ በሁለቱ ወገኖች መካከል ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲረዳ እንደ ማበረታቻ የቀረበ ነው።

የካቲት 28 አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸሙት የአየር ጥቃት ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የዓለምን 20 በመቶ የነዳጅ አቅርቦት የሚያስተላልፈው ይህ የባህር መስመር ተዘግቶ የቆየ ሲሆን፥ ይህም ዓለም አቀፍ የኢነርጂ ቀውስ አስከትሏል።

ትራምፕ በማህበራዊ ድረ-ገጻቸው ላይ ‹‹እገዳው ሙሉ በሙሉ እንደቀጠለ ሆኖ፣ ስምምነቱ ተጠናቆ ሊፈረም የሚችል መሆኑን ለማየት ‘ፕሮጀክት ፍሪደም’ የተባለው እንቅስቃሴ ለጥቂት ጊዜ እንዲቆም በጋራ ተስማምተናል››በማለት ፅፈዋል::

ይህን የትራምፕን ጽሁፍ ተከትሎ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.2 በመቶ ቀንሶ በአንድ በርሜል 108.60 ዶላር ሆኗል።

የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት ነዳጅ ዋጋም እንዲሁ በ1.2 በመቶ ቀንሶ 101.06 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።

ኋይት ሀውስ ምን ዓይነት መሻሻል እንደተገኘ ወይም የተጠቀሰው እረፍት እስከ መቼ እንደሚቆይ ለቀረበለት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና ሌሎች ከፍተኛ የአስተዳደሩ ባለስልጣናት እንደተናገሩት፤ኢራን በወሽመጡ በኩል ያለውን ትራፊክ እንድትቆጣጠር ሊፈቀድላት አይገባም።

ኢራን ፈንጂዎችን፣ ድሮኖችን፣ ሚሳኤሎችን እና ፈጣን የጥቃት ጀልባዎችን በመጠቀም ስትሬቱን ዘግታለች፡፡

አሜሪካ በበኩሏ የኢራን ወደቦችን በመዝጋት እና ለንግድ መርከቦች የታጀበ ጉዞ በማዘጋጀት ምላሽ ሰጥታለች።

ሀና ሰይፉ

ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...