
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ ከአሜሪካ ጋር የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ የሚደረግ ቀጥተኛ ድርድር “ትርጉም የለሽ” ሲሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ገልፀውታል።
ትራምፕ ባለፈው ወር ለኢራን መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ በላኩት ደብዳቤ ቴህራን ኒውክሌር መርሃግብሯ ጋር በተገናኘ ድርድር እንድታደርግ አለበለዚያ ግን ከፍተኛ ወታደራዊ እርምጃ ይጠብቃታል ማለታቸው የሚታወስ ነው እንደ አልጀዚራ ዘገባ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው “ድርድር ከፈለግክ ማስፈራራት ፋይዳው ምንድን ነው?” በማለት የዋሽንግተን የድርድር ጥያቄ ቅንነት የሌለው ሲሉ አጣጥለውታል ።
ቴህራን ከዚህ ቀደም ከዋሽንግተን ጋር ቀጥተኛ ውይይትን ውድቅ አድርጋለች፡፡ ይሆን እንጂ ተዘዋዋሪ ድርድርን ግን ክፍት እንደሆነ ተናግራለች።