ኢትዮጵያ ሚዲያ የልህቀት ማዕከል በይፋ ተከፈተ

Date:



በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አማካኝነት የተለያዩ የጋዜጠኝነት አይነቶችን አካቶ ለዘርፉ ሙያተኞችን ለማሰልጠን የሚያስችለውን የሚዲያ ልህቀት ማዕከል መክፈቱ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

በዚህ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል የምስረታና የስራ ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ ከተገኙ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መካከል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕ/ተ/ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሞዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ፣የመገናኛ ብዙሃን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር)ን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።

በዚሁ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ምስረታና መክፈቻ ስነ -ስርዓት ላይ የታደሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕ/ተ/ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የማዕከሉ ምስረታ ሚዲያው ኢትዮጵያን የሚመስል ስራ የሚሰራ በዘርፉ የበቁና ፍቃድ ያለው ባለሙያን ለማሰልጠን ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሚዲያ የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊነት ያስጠበቀ መሆን ይገባል ሲሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሞዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አሳስበዋል።

የግልና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በብሄራዊ ጥቅም ላይ ልዩነት ሊኖር የለበትም ብለዋል።

በሚቀጥሉት ጊዜያት ጋዜጠኝነት የሙያ ብቃትና ፍቃድ የሚሰጠው ዘርፍ ይሆናል ሲሉ ገልፀው፤ ለዚህም ይህ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ማዕከሉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕ/ተ/ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ተመርቆ በይፋ ተከፍቷል።

NBCEthiopia

ሆኖ_መገኘት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...