“ኢትዮጵያ በአመት የማር ምርት 10 በመቶውን ብቻ ነው የምታመርተው”-  ጥናት

Date:

ኢትዮጵያ በአመት የማር ምርት የማምረት አቅሟ 500 ሺህ ቶን ቢሆንም በዘርፉ ባሉ ተግዳሮቶች 10 በመቶውን ብቻ እንደምታመርት አንድ ጥናት አመላከተ።

ጥናቱን ያጠኑት በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ እና የእንስሳት ፖሊሲ ምርምር ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ ሲሆኑ 22 የዘርፉ ተዋናኞች ተካተውበታል።

ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ በኢትዮጵያ የንብ አረባቡ እና አመራረቱ 92 በመቶ የሚካሄደው በባህላዊ ዘዴ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ዶክተር ደሳለኝ ቤኛ በዝርዝር ምን አሉ ?

የዓለም የማር ፍላጎት እየጨመረ ቢመጣም ኢትዮጵያ ጥራት ባለው የግብአት አቅርቦት ውስንነት፣ በቂ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ እና ለንብ አናቢዎች በቂ ሥልጠና ባለመሰጠቱ ማምረት ከሚገባት በጣም ዝቅተኛ እያመረተች ትገኛለች።

ደረጃቸውን የጠበቁ የምርት ጥራት ማረጋገጫ ዘዴዎች አለመኖራቸው በዓለም ገበያ ያላትን ተወዳዳሪነትም በእጅጉ እየጎዳው ነው።

በጥናቱ ማረጋገጥ እንደተቻለው የምናመርትበት ቴክኖሎጅ የችግሩ መንስኤ ነው። የንብ አረባቡ እና አመራረቱ 92 በመቶ የሚኣሄደው በባህላዊ ዘዴ ነው። ይህ ደግሞ ለአመራረት ምቹ አይደለም።

ምክንያቱ ደግሞ ማሩ ሲቆረጥ የሞቱ ንቦች አብረው ይቀላቀላሉ፣ የማሩ እንጀራ እና  ማሩ አንድ ላይ ይሰባበራል። ጥራቱንም በእጅጉ እየጎዳው ነው።

ለማምረቻ እና ለምርት ውጤቶች የሚሆኑ የግብአት አቅርቦት የለም፣ ያሉትም ጥራታቸው ከፍተኛ ችግር አለበት።

ምርቱም ምግብ ነክ በሆኑ እና ባልሆኑ እንደ ስኳር ባሉ ነገሮች እየተከለሰ ለገበያ እየቀረበ ነው። በጥራት ጉድለት ላኪዎችም በአለም አቀፍ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ አለመሆናቸውን በግልፅ አስቀምጧል።

በዘርፉ የተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች የራሳቸውን ፕሮጀክት አላማ ወይም ሪፖርታቸውን ለማሳካት ብቻ ነው የሚሰሩት። ይህ ደግሞ ዘርፉን እየፈተነው ነው።

የአረባብ ዜዴውን ማዘመን፣ ለአምራቾች የቴክኖሎጅ አጠቃቀምን ማስተማር፣ የፀረ ተባይ ኬሚካሎችን አጠቃቀም ግንዛቤ መስጠት፣ በዘርፉ ያሉ ፖሊሲዎች ተግባራዊ የሚሆኑበትን ሁኔታ መፍጠር አስፈላኪ መሆኑን ገልፀዋል።

የላኪዎችን አቅም ማሳደግ እና ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ አርሶ አደሮችን በማሰባስብ እንድያመርቱ ማድረግ፣ የማር ምረት መያዣ እቃዎችን ጥራት ማሳደግ፣ ባለሀብቶችን ወደ ዘርፉ ማምጣት ለችግሮቹ መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...