ኢትዮጵያ በዓለም የደስታ ሪፖርት ከ147 ሀገራት 135ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

Date:

​ ይፋ የሆነው የ2026 የዓለም የደስታ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ 147 ሀገራት መካከል 135ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ይህ ውጤት ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ የኑሮ ውድነት እና ማህበራዊ ጫናዎች ጋር ተዳምሮ የዜጎችን የደስታ ስሜት ዝቅ እንዲል ማድረጉን ያሳያል።

ሪፖርቱ ኬንያን በ110ኛ እንዲሁም ሶማሊያን በ117ኛ ደረጃ ላይ  አስቀምጧቸዋል።

ፊንላንድ ማንንም ሳታስጠጋ ለ9ኛ ተከታታይ ዓመት የዓለም ደስተኛዋ ሀገር በመሆን ክብረ ወሰን ስታስመዘግብ፣ እንደ አይስላንድ እና ዴንማርክ ያሉ የሰሜን አውሮፓ ሀገራት ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

የዘንድሮው ሪፖርት ትልቁ መነጋገሪያ ግን ኮስታሪካ ናት፤ ሀገሪቱ በጠንካራ ቤተሰባዊ ትስስር እና ማህበራዊ ሰላም ምክንያት ከነበረችበት 23ኛ ደረጃ ተነስታ 4ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ዓለምን አስገርማለች።

​በሌላ በኩል ሪፖርቱ በወጣቶች ላይ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ሱሰኝነት ምክንያት የሚመጣ የደስታ ማጣት ዓለም አቀፍ ስጋት መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል።  አፍጋኒስታን እና ሴራሊዮን በደረጃው ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...