ኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቀሌ ምን ገጠመዉ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET-298 በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከአውሮፕላን መንደርደሪያው መጠነኛ የመንሸራተት እክል አጋጥሞታል። አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜ ዝናብ እየዘነበ ነበር።

እስካሁን ባለን መረጃ በክቡራን መንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰና በሰላም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ የተደረገ ሲሆን በሁለት የበረራ ሰራተኞቻችን ላይ መጠነኛ ጉዳት በማጋጠሙ ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም ተወስደው ከታከሙ በኋላ ወደ ሆቴል እንዲሄዱ ተደርገዋል።

ምንግዜም ለደንበኞች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ እየጠየቀ ተጨማሪ መረጃ ሲኖር ለክቡራን ደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑን በአክብሮት ይገልፃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...