መኖር ከማይችል ሰው ግብር አትሰበስብም ፤ በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አትሰበስብም

Date:




” እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብ አለበት ልማትም መቀጠል አለበት ፤ የሰው ህይወትም መቀጠል አለበት ፤ ሰው እየተራበ መስራት አይችልም ምርታማ መሆን አይችልም ! “

የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ስለ ገቢ ግብር አዋጁ ምን አሉ ?

” የደመወዝ ገቢ ግብር ከዚህ በፊት መነሻው 600 ብር ነው፤ አሁን በረቂቁ የቀረበው 2,000 ሆኖ ነው።

በመሰረቱ 600 በሆነበት ሰዓት አንደኛ ገንዘብ የመግዛት አቅሙ ትልቅ በመሆኑ ፣ 1 ዶላርም 20 ብር ነበር ያኔ የዛሬ 10 ዓመት አካባቢ ነው ይሄ ነገር የተሻሻለው ፤ ሁለተኛ የመንግሥት ሰራተኞች መነሻ ደመወዝ 600 ነበር ያኔ 600 ለአንድ ሰው ለአንድ ወር ቢያንስ ምግብ መብላት ብቻ ይበቃዋል በሚል ታሳቢ አማካይ ተወስዶ ነው 600 የተባለው።

አሁን ግን 300% ፣ 200% ጨመርን (ማለትም 2000 ብር አደረግን) እሱ አይደለም ዋናው መነሻው ስንት ነው አሁን ? በአጭሩ ፤ እንኳን የኑሮ ውድነቱን ታሳቢ ያደረገ መንግሥት እራሱ ሰራተኛው በ600 ብር ሊያኖረው አይችልም ፤ የኑሮ ውድነቱ ከሚታሰበው በላይ በተለይም በሪፎርሙ መንግሥት በይፋ ያረጋገጠው ታችኛው የሰራተኛ ክፍል ጎድቶታል፤ ‘ ሊቋቋመው አይችልም ‘ በሚል መነሻ ደመወዙን ከፍ አድርጓል ፤ መነሻ ደመወዝን ከፍ ሲያደርግ ይሄን ታሳቢ አድርጓል።

አሁንም ቢሆን እነዚህ ሰዎች መኖር ከማይችል ሰው ግብር አትሰበስብም ፤ በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አትሰበስብም። በቀን 2.15 ዶላር የሚያገኝ ሰው ድሃ ነው ከዚያ በታች የሚያገኝ በሙሉ ድሃ ነው ፤ እኛ ደግሞ እዛ ሁሉ አልደረስንም።

እኛ እያቀረብን ያለነው ሃሳብ 8,324 መነሻ ይሁን ነው። እንኳን የኛ ሀሳብ የመንግሥት እራሱ ያስቀመጠው መነሻ ላይ እንኳን አልደረሰም።

ሌላው በፊት የግብር ምጣኔው ከ0 ጀምሮ 10% ፣ 15% ፣ 20% ፣ 25% ፣ 30% ፣ 35% ይቀጥል ነበር አሁን 10%ን ከመሃል አወጡና ከ0 ጀምረው ቀጥታ 15% ነው የገቡት። አሁን ቀጥታ ከ15 ከከፍተኛው ነው ሲጀምር የጀመሩት። ይሄ ትክክል አይደለም።

35% ከየት ጀመረ 14,100 በላይ የሚያገኝ ሰው 35% ግብር ይከፍላል ፤ 35% ከሰራተኛ በአሁኑ የኑሮ ውድነት 15% በእያንዳንዱ በምግብ ዋጋም፣ በሚገዛው እቃም 15% ይጨምራል ይሄ ሲደመር 50% ይመጣል፤ 7% የጡረታ አለ ጡረታ የሚያገኘው ከ60 ዓመት በኃላ አሁን ግን 57% ከደመወዙ ላይ ይሄዳል በቀረችው 43% ፦
– ልጆች ያስተምራል
– ምግብ ይበላል
– ልብስ ይገዛል
– ቤት ይከራያል ምንድነው የሚያደርገው ?

ይሄና ይሄ ብቻ ስላልሆነ ነው ዝም ያልን እንጂ ይሄም ከፍ ብሎ እኮ ይበቃል ማለት አይደለም።

ግን እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብ አለበት ልማትም መቀጠል አለበት ፤ የሰው ህይወትም መቀጠል አለበት ፤ ሰው እየተራበ መስራት አይችልም ምርታማ መሆን አይችልም። “

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...