“ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ አቅም መፍታት ይጠበቅባታል”

Date:

ኢትዮጵያ በዓለም እንዲሁም በጎረቤት ሀገራት ለሚነሱ ግጭቶች ሰላም አስከባሪዎችን የምልትክ ትልቅ ሀገር እንደመሆኗ፤ ውስጣዊ የሰላም ችግሮቿን በራሷ አቅም መፍታት ይጠበቅባታል ሲሉ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የእስራኤል ምክር ቤት አባል ጸጋ ፋንታሁን (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በእስራኤል ፓርላማ ውስጥ አባል ከሆኑ ሦስት ቤተ-እስራኤላውያን ውስጥ አንዷ የሆኑት ጸጋ ፋንታሁን (ዶ/ር)፤ በእስራኤል ጉብኝት በማድረግ ላይ ከሚገኙትና ከኢትዮጵያ የተለያዩ ሚዲያዎች ከተውጣጡ ከፍተኛ ኤዲተሮች ጋር በእስራኤል ፓርላማ ውስጥ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ላይም ከ175 ሺሕ በላይ ቤተ-እስራኤላውያን በእስራኤል ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 83 ሺሕ የሚሆኑት እስራኤል ውስጥ የተወለዱ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም በእስራኤል ፓርላማ ውስጥ ከሚገኙ 120 አባላት ውስጥ ሦስት ቤተ-እስራኤላውያን እንደሚገኙ የገለጹት ዶ/ር ጸጋ፤ በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በውትድርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በሕክምና፣ በፍርድ ቤቶች እና በሌሎች የስራ ዘርፎች በርካታ ቤተ-እስራኤላውያን ተሰማርተው እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አሁን ያለውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ ከከአሐዱ ለተነሳላቸው ጥያቄ የምክር ቤቱ አባል ሲመልሱ፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር መሆናን እና አቅም እንዳላት አንስተው አሁን ላይ በፖለቲካዊ መከፋፈል ያ የቀደመ አቅሟ እየተዳከመ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ስለሆነም ሀገሪቱ ሁሉንም ሃይሎች ወደ አንድ የሰላም መድረክ በማምጣት፤ መከፋፈልን ወደ ሰላም እንዲሁም ግጭትን ወደ መተባበር መቀየር ይገባታል ብለዋል፡፡

የእስራኤልን ፖለቲካን እንደምሳሌ ያነሱት ዶ/ር ጸጋ፤ “እስራኤል ዴሞክራሲያዊ ሀገር እንደመሆኗ ከ120 የፓርላማ አባላት መካከል 10ሩ የእስራኤል ዜጋ አረቦች ናቸው፤ በተጨማሪም አክራሪ ሃይማኖተኞች፣ ብሄራዊ የእምነት ተቋማት ተወካዮች እና ግራ ዘመምም ፖለቲከኞችን ጨምሮ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ያካተተ ነው” ብለዋል፡፡

“አንዳንድ ጊዜ የመንግሥት በማዋቀር ውስጥ ችግር ያመጣብን የፓርቲዎቹ ብዛት ነው ፓርቲዎቹ ሲበዙ እያንዳንዱ የራሱን ጥቅም ማስከበር ይፈልጋል” ያሉም ሲሆን፤ ስለዚህ በኢትዮጵያም የፓርቲዎች መብዛት ሳይሆን ጠንካራ መንግሥት ለመመስረት በጋራ የሚቆም እንደሚያስፍልግ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የሚገኙ ሚዲያዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ስለግጭት እና ሰላም ማጣት ብቻ ሳይሆን፤ ‘ስለ አንድነት እና መተባበር እንዲሁም ውስጣዊ ችግሮችን እንዴት መፍታት ይቻላል’ በሚለው ጉዳይ ላይ ይበልጥ ትኩረት ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

በሊዲያ አበበ (ከእስራኤል እየሩሳሌም)
አሐዱ ራዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...