ኤል አዉቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ እና “ሙንጃ ግሩፕ” የኖርዌይ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ህዳር 11/2018 ዓ.ም ተፈራርሟል።
የሁለቱ ድርጅቶች የጋራ ስምምነት በአሁን ሰአት የሀገራችንን የትራንስፖርት ፍላጎት እያደገ መምጣቱን ታሳቢ በማድረግ ከኖርዌይ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅት ጋር ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ በአንድ ጊዜ 500 የተለያዩ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማስመጣት እና ለመገጣጠም እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።
ስምምነቱ በዋናነት ያተኮረው በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እና ያረጁ ታክሲዎችን በአዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለመተካት እንደሆነም ተገልፆ በአሁኑ ሰዓት ወደ 8ዐዐ የሚጠጉ መኪኖች በመገጣጠም ሂደት ላይ ሲሆኑ፣ የወረቀት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑም የኤል አዉቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ መስራች አቶ ቶኪቾ አለማየዉ ገልፀዋል።
