ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም ሲሉ የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አስታወቁ

Date:

“የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አለ” የሚለውና ተደጋጋሚ የሆነ በተወሰኑ አካላት የሚነሳ ውንጀላ ፍፁም ሀሰት እና ግጭት ለመቀስቀስ ምክንያት ለመፍጠር ነው፤ የኤርትራ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ በሉዓላዊ ግዛታቸው ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲሉ አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል።

ሚኒስተሩ አክለው ከዚህ ቀደም በብዙ አጋጣሚዎች በማያሻማ መልኩ እንደተገለጸው፣ ኤርትራ የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም፤ በመሰረቱም ስምምነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ኤርትራ በህወሓት የፖለቲካ አንጃዎች ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት የላትም ይህም በትግራይ ህዝብ ላይ አላስፈላጊ እና ሊወገድ የማይችል ስቃይ ያስከትላል ብለዋል።በቀይ ባህር ዙሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ሌት ተቀን የሚያወጡት የማያቋርጥ ግጭት ቀስቃሽ መግለጫዎች ለአላስፈላጊ ውጥረቱ አባባሽ ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል ያሉ ሲሆን ይህ ያለምንም ማወላወል በጠንካራ ሁኔታ መወገዝ አለበት ሲሉም የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አቶ የማነ ገብረመስቀል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ተቋም ላይ ጥቃት ለማድረስ ዛቱ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዝዳንት...

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካ ” American Space ” ማዕከል ተመረቀ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቨን ማሲንጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመውን "American...

አሐዱ ባንክ ለ 8ኛ ጊዜ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

አሐዱ ባንክ ሥራ የጀመረበትን 4ኛ ዓመት በማስመልከት የተለያዩ ኩነቶችን...

ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት...