ኤፍቢአይ መቀመጫቸውን ኢራን አድርጎ በአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ የሳይበር ጥቃት፣ የመረጃ ምዝበራ እና ምንተፋ የሚያካሄድ ቡድን የሚገለገልባቸውን አራት ድረ ገጾች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።
የአሜሪካ የፍትህ ቢሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው “የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የስለላ እና የደህንነት ሚኒስቴር የሚያካሄደውን የመረጃ ብርበራ እና የድንበር ተሻጋሪ ምንተፋ እቅዶችን ለማደናቀፍ የሚደረገው ቀጣይነት ያለው ጥረት አካል ነው” ብሏል።
የፍትህ ቢሮ እንዳስታወቀው፣ የተያዙት ድረ ገጾች ጋዜጠኞችን፣ የአገዛዙን ተቃዋሚዎች እና የእስራኤልን ሕዝብ እንዲገደሉ ጥሪ ይተላለፍባቸው ነበር ብሏል።
“ኢራን አሜሪካውያንን ለማሸበር እና ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘት የሐሰት ድረ ገጾችን እና ኪቦርድ ጀርባ ልትደብቅ እንደምትችል አስባ ነበር” ሲሉ የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል ተናግረዋል።
“የዘመቻቸው አራቱን ምሰሶዎች አፍርሰናል፤ አልጨረስንም” ያሉት ፓቴል “ኤፍቢአይ ከእነዚህ ፈሪ የሞት ዛቻዎች እና የሳይበር ጥቃቶች በስተጀርባ ያሉትን ሁሉመም ተዋናዮች ያድናል፤ እንዲሁም የአሜሪካን የሕግ አስከባሪ ኃይሎች ሙሉ ኃይል በእነሱ ላይ ያዘምታል” ብለዋል።
