አራት ባንኮች የብሔራዊ ባንክን ‹‹ከባድ›› የብድር ጫና የመቋቋም አቅም ግምገማ ማለፍ አልቻሉም

Date:

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሥርዓት ከፍተኛ የብድር ጫና ቢያጋጥመው አራት ባንኮች በሕግ ከተቀመጠው የካፒታል መጠን በታች እንደሚወርዱና 8.3 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ካፒታል እንደሚያስፈልጋቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው የፋይናንስ መረጋጋት ሪፖርት ገለጸ።

በፋይናንስ ተቋማት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የኢኮኖሚ ድንገተኛ ሥጋቶችን የመቋቋም አቅማቸውን የገመገመው ብሔራዊ ባንክ በሪፖርቱ፣ የባንክ ኢንዱስትሪው በአጠቃላይ የተረጋጋ ቢሆንም በአንዳንዶች ላይ ግን በከባድ ሁኔታ ተጋላጭነት መኖሩን አስታውቋል፡፡

‹‹የብድር ሥጋት መቋቋም ግምገማው (Credit Stress Tests) እንደሚያሳየው፣ ሁሉም የንግድ ባንኮች በመካከለኛ ጫና ውስጥ ያለ ምንም ተጨማሪ ካፒታል መደበኛ ሥራቸውን ለመቀጠል የሚያስችል አቅም አላቸው። ሆኖም በከባድ ጫና አራት ባንኮች ፈተናውን ያላለፉ ሲሆን፣ እነዚህም በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 8.3 ቢሊዮን ብር ወይም ለሥጋት ተጋላጫ ሀብታቸው (Risk Weighted Assets) 1.5 በመቶ የሚሆን ተጨማሪ ካፒታል ያስፈልጋቸዋል፤›› ብሏል።

ይህ የብድር ጫና ግምገማ (Credit Risk Stress Test) የተከናወነው፣ የተበላሹ ብድሮች (NPLs) አሁን ካሉበት ደረጃ በእጅጉ አሻቅበው (Severe) 30 በመቶ ላይ ቢደርሱ ሊፈጠር የሚችለውን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ነው።

በብሔራዊ ባንክ ሪፖርት እንደተመላከተው ባንኮች የፋይናንስ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት…

🔗 ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/153613/

ከሪፖርተር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...