እሰራኤል ለሶማሌላንድ ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ አገር ሆነች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሀርጌሳ ዕውቅና ሰተናል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ሶማሌላንድ ከሶስት አስርት ዓመታት በሁዋላ የአገርነት ክብርና እውቅናን ማግኘቷ ለቀጠናው ፖለቲካ ወሳኝነት አለው ተብሏል።
ሶማሌላንድ በምላሹ ለእስራኤል ዕውቅና ሰታለች።
በአብረሃም ስምምነት መሰረት የሆነ ነው በሚል ኔታንያሁ ጉዳዪን በበጎ ዓለም ልትወስደው ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል።
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመጀመር የጋራ ድንጋጌም አውጥተዋል።
እስራኤል በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ ዕቅድ መሰረት የሆነ ነው በሚል ስምምነቱን ዓለም አቀፋዊ አንደምታ ሰታዋለች
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
