እስራኤል በቴህራን የፕሬዝዳንቱን ፅሕፈት ቤት ደበደበች

Date:

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በተሸጋገረበት በዚህ ወቅት፥እስራኤል በኢራን መዲና ቴህራን በሚገኘው “የመሪዎች ቅጥር ግቢ” እና በፕሬዝዳንቱ ፅሕፈት ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች።

ከቅዳሜ ጀምሮ በቴህራን “እያንዳንዱ የከተማዋ ክፍል” ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን የዐይን እማኞች እየገለጹ ነው።

አዳዲስ የወጡ ምስሎችም በከተማዋ ምስራቃዊ አቅጣጫ ግዙፍ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን ያሳያሉ።

የቀይ ጨረቃ ባወጣው መረጃ መሠረት፥ የአሜሪካና የእስራኤል ጥቃት ከተጀመረ ወዲህ በኢራን የሟቾች ቁጥር 7መቶ87 ደርሷል።

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከኢራን በተነሱ ሁለት ድሮኖች መመታቱ ተረጋግጧል።

በሌላ ግንባር እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምድር ወረራዋን እንደምታሰፋና “ተጨማሪ ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ለመቆጣጠር” ወታደሮቿ ወደፊት እንደሚገሰግሱ አስታውቃለች።

ግጭቱን ተከትሎ የዓለም አቀፍ የጋዝ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየናረ ይገኛል።

ሰኞ ዕለት የ50 በመቶ ጭማሪ የታየ ሲሆን፥ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ ተጨማሪ የ30 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...