ኦፌኮ ከተመድ ጋር በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ተወያየ

Date:

የኦሮሞ ፌዴራላሲት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በ2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ዙርያ ውይይት ማድረጉን አስታወቀ።

በኦፌኮ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም የተገኙ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር የሆኑት አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን ጨምሮ አራት አባላትን የያዘ ልዑክ መገኘቱን ከፓርቲው ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኦፌኮ በስብሰባው ላይ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ መንግስት ሊያሟላቸው የሚገቡ “መሰረታዊ” ጥያቄዎችን ማቅረቡ ተጠቁሟል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ላይ መሳተፉ ሙሉ በሙሉ “በመሠረታዊ እና በተጨባጭ ለውጦች” ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ሐምሌ 6 ቀን...

በሳውዲ ከ1900 በላይ ኢትዮጵያዊ እስረኞች በምህረት ተለቀቁ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ በሳዑዲ...

“የሟችም የገዳይም እናት እኔ ነኝ”

​"የሟችም የገዳይም እናት እኔ ነኝ" በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ...

የአዲስ አበባ የ2019 በጀት 502.27 ቢ. ብር ሆኖ ፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት...