ከአንድ ተቋም የተባረረ ተማሪ የቀድሞ ውጤቱ አይያዝለትም

Date:

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካዳሚክ  ምክንያት ለተባረረ (dismissed) ተማሪ የኮርስ ኤግዘምሽን በተመለከተ አዲስ መመሪያ በላከው ደብዳቤ አስታውቃል።

ባለስልጣኑ በሚኒስትሮች ምክርቤት በወጣ ደንብ ቁጥር 515/2014 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ እና ለመከታተል ስልጣን ተሰጥቶታል።

በተሰጠው ስልጣንም በመመሪያ 987/2016 ዓ.ም አንቀፅ 13 ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት ማንኛውም ተቋም ስልጣን ባለው አካል የወጣ የቅበላ መስፈርት ያለሟሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደማይቻል ደንግጓል፡፡ አንድ ተማሪ በአካዳሚክ ምክንያት ከአንድ ተቋም በሚባረርበት ጊዜ ተማሪው ብቁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው።

በዚህም ተማሪው በአዲስ መልክ ሌላ ተቋም ውስጥ በትምህርት ዘመኑ በተቀመጠው የመቁረጫ ነጥብ ውጤት የሚያስገባው ከሆነ ተመዝግቦ ቢማር ቀድሞ በተባረረበት ተቋም በአንዳንድ ኮርስ ያገኘው ውጤት ኤግዘምት የማይደረግ በመሆኑ ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማሳስቢያ ተሰጥቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከባድ ሙስና የተከሰሱትን 4 ተከሳሾችን፤ ፖሊስ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ቀረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ የ'ይፈለጋሉ" ማስታወቂያ የወጣባቸው...

ስለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ውጥረት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ...

የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ...

ፔንታጎን የእስራኤል ስለላ እንደሚያሳስበው ተገለጸ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፔንታጎን እስራኤል ከፍተኛ ልዑኮችን ጨምሮ የአሜሪካ...