ከፋታ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተቋም ለ 38ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በትላንትናው ቀን አስመረቀ

Date:

የከፋታ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተቋም ለ 38ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በትላንትናው ቀን ግንቦት-10-2017 ዓ.ም በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አስመርቋል።

“ውበት በልዩነት በጋዜጠኝነት” በሚል መሪ ቃል የምረቃ ስነ-ስርዓታቸውን በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ የተማሩትን ትምህርት በተግባር መድረክ ላይ በተለያዩ ፕሮግራሞች ለእንግዶች በማቅረብ አካሂደዋል።

በፕሮግራሙ ላይም አንጋፍ ጋዜጠኞች ተጋባዥ እንግዶች መምህራን እና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ተጋባዥ እንግዶች እና መምህራንም ለተመራቂ ተማሪዎች የ አደራ መልዕክት እና ምክር አስተላልፈዋል።

ከፋታ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተቋም በ 6 ወር የስልጠና ጊዜ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና በመስጠት ተማሪዎችን አሰልጥኖ በሙያዉ ብቁ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...