ባለስልጣኑ ይህንን ያለው የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነው።
የተወገዱት ምግቦችም በአብዛኛው የታሸጉ ምግብና መጠጦች ሲሆኑ በአቀማመጥ ምክንያት ለከፍተኛ የፀሃይ ብርሃን የተጋለጡም እንደሚገኙት በባለስልጣኑ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጅራ ነግረውናል።
በተጨማሪም በህገወጥ መደሃኒት ቁጥጥር ግምታዊ ዋጋው ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ 10 ኪሎ ግራም የተጠጋ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈ መድሀኒት መወገዱንም ጠቅሰዋል ::
የምግብና ጤና ነክምርቶች ማስወገድ የተቻለ ሲሆን 310 በሚሆኑ ከስታንዳርድ በታች ሲሰሩ በተገኙ ተቋማት ላይ እርምጃ ወስዷል::
በተጨማሪም በ158 የሚሆኑተቋማቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል ተብሏል::
ህብረተሰቡ በሸመታ ወቅት የምርቶችን የመጠቀሚያ ጊዜ እየተመለከተ መሸመት አለበት ያሉት አቶ ገልገሎ ችግሮች ሲያጋጥሙ ጥቆማ ማህበረሰቡ ጥቆማ በመስጠት ቢተባበር ሲሉም ጠይቀዋል።
