ከ50 ሺሕ በላይ በነፃ ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል አስታወቀ

Date:

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ጡረታ የወጡትን እንዲሁም አጠቃላይ የፌዴራልና ክልል የፖሊስ አባላትንን ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ፤ በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ያለምንም ክፍያ የነፃ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ በዓመት ከ50 ሺሕ በላይ ለሚሆኑት የተኝቶ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት በሆስፒታሉ የጤና አገልግሎት ዋና መምሪያ ረዳት መኮንንና የፅ/ቤቱ ኃላፊ ዶክተር ናሆም ፀሀይ፤ በየቀኑ ከ500 እስከ 700 የሚደርሱ ታካሚዎችን እንደሚያስተናግድ ለአሐዱ ተናግረዋል።

የሚሰጡ ሕክምናዎችን በተመለከተም ሆስፒታሉ በዋናነት የፖሊስ ስርዓት ውስጥ ያለ እንደመሆኑ መጠን፤ በብዛት የሚሰሩ የቀዶ ሕክምናና የአጥንት ሕክምና አገልግሎቶች እንደሆኑ አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተመላላሽ ሕክምና ባለፋት 6 ወራት ውስጥ ብቻ በትንሹ ከ50 ሺሕ በላይ ለሚሆኑት አገልግሎት መሰጠቱን የገለጹት ዶክተር ናሆምለ ከእነዚህ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የእናቶችና ሕጻናት ሕክምና እንደሆነ አክለዋል።

ሆስፒታሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በሚገኝበት ቦታዎች በሙሉና በ115 ክሊኒኮች አማካኝነት ለአባላቱ ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹም ሲሆን፤ አንዳንድ ክሊኒኮችም ከፖሊስ ስርዓት ውጪ የሆኑ መደበኛ ዜጎች ጭምር የሚጠቀሙበት እንደሆኑ ተናግረዋል።

ከተመሰረተ 62 ዓመታት የሆነውና መቀመጫውን ሜክሲኮ (ልደታ) አካባቢ ያደረገው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የአዕምሮ ቀዶ ሕክምናን መስጠቱን አንስተዋል።

አክለውም ከዚህ ቀደም ታካሚዎች በሆስፒታሉ የሌሉ መድኃኒቶችን ከውጪ ጤና ተቋማት በኩል እንዲገዙ በማድረግ ሂሳብ የሚወራረድበት አግባብ እንደነበረ ጠቅሰው፤ ይህ የሚፈጥረውን ውጣ ውረድ ለመቀነስና መድኃኒቶችን በአጭር መንገድ እንዲያገኙ ለማስቻል በሆስፒታሉ ውስጥ ማንኛውም ማህበረሰብ ሊገለገልበት የሚችል ፋርማሲ መከፈቱን አስታውሰዋል።


#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...