ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል

Date:


የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡

የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸሙ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የቀረበ ሲሆን፤ በዚህም በተያዘው የ2017 የትምህርት ዘመን 26,789,407 ተማሪዎች ተመዝግበው በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ በሪፖርቱ ሲገለጽ፤ በተቃራኒው በሀገር አቀፍ ደረጃ5 ሺህ3 መቶ 54 ት/ቤቶች በሰውና በተፈጥሮ  በደረሰባቸው አደጋ አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው ተብሏል፡፡

ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ከሚሆኑት  ውስጥ 48.2 በመቶ  ሴቶች መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡በትምህርት ዘመኑ ከአንደኛ ደረጃ እስከ 8ተኛ ክፍል ድረስ ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑትን ለመመዝገብ ታቅዶ 33 ነጥብ 7 በመቶ ማሳካት መቻሉንም የሚኒስቴሩ ሪፖርት አመልክቷል፡፡

በሪፖርቱ ከተዳሰሱ ክንውኖቹ  መካከል ለሁለት አመታት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በአማራና በአፋር ክልሎች የሚገኙና አደጋ ደረሰባቸው ት/ቤቶች የመልሶ ግንባታ ወይም ጥገና እንደሚገኝበት መገለጹን አሻም ከሪፖርቱ መመልከት ችላለች፡፡



አሻም
ቲቪ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...