በምርጫ ቦርድ ፈቃድ አግኝቶ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የጉሙዝ ህዝብ ዴሚክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ፓርቲ አመራሮች መታሰራቸውን የክልሉ ምክር አባል ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ም/ቤት አባልና የዛይ ወረዳ ምርጫ ክልል ተወካይ አቶ ለሜሳ ኔኖ፣ “ወረዳ ላይ ካሉ ስምንት አመራሮች አምስቱ ታስረዋል፤ ሦስቱም እየተፈለጉ ነው፡፡ ቀበሌ ላይ በወረዳ ኮንፍረንስ የተሳተፉም ‘ይታሰራሉ’ ተብሎ የጥሪ ደብዳቤ እያተዘጋጁ እንደሆነ ነው መረጃ የደረሰኝ” ብለዋል።
የምክር ቤት አባሉ በዝርዝር ምን አሉ ?
“ ሕጉም አዋጁም በሚለው መሰረት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለአካባቢው መስተዳደርና ጸጥታ አካላት በማሳወቅ ድርጅታዊ ኮንፍራንስና የአባላት ውይይት ማድረግ አላቸው፡፡ ይህንን ሲደረግም ለአካባቢው አካላት ማሳወቅ አለባቸው የሚል እንደ ግዴታም ተቀመጠ አሰራር አለ፡፡
ነገር ግን የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በቀን 28/2017 ዓ/ም በከማሽ ዞን ዛይ ወረዳ ኮንፍረንስ እንናካሂዳለን ብለን ለአካባቢው አስተዳደር በደብዳቤ ተጠይቆ የማሳወቅ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ለአካባቢው ጸጥታ አካላትም አሳውቀናል፡፡ አስተዳደሮች ጥያቄውን ባይባቀበሉትም በጸጥታ አካላቱ ተቀባይነት ኮንፍረንሱ ተካሂዷል፡፡
ከንፈረንስ ተካሂዶ ውሎ ካደረ በኋላ ትላንት ‘ኮንፍረንስ ለምንድንነው ያካሄዳችሁት?’ ብለው የዛይ ወረዳ ጉህዴን አመራሮችን አስረዋቸዋል፡፡ ህጋዊ ድርጅት ላይ እንዲህ ማድረግ አግባብ አይደለም፡፡ ለማን አቤት እንደምንልም ግራ ገብቶናል።
ለክልል ጸጥታ ቢሮ፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለዞን ጸጥታ መምሪያ አሳውቀናል፤ ግን አልተፈቱም፡፡ አመራሮቹ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ ጉዳዩ ቶሎ መፍትሄ ካልተሰጠው ደግሞ ችግር ሊነሳ ይችላል።
ህዝቡ ለጉህዴን ድምጽ ይሰጣል ተብሎ የማደናቀፍ ሥራ ነው እየተሰራ ያለው ወረዳው። ወንጀል የሰራ አካል በሕግ መጠየቅ አለበት፡፡ ነገር ግን በፓርቲ ስም ብቻ የሚደረጉ ማሰርና ማሳደዶች ችግር ያመጣሉ።
የድርጅት አባል ውይይት የማድረግ መብት አለው፤ ውይይት ሲያደርግ ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት ይላል የምርጫ አዋጁ” ያሉት አቶ ለሜሳ፣ “ግን ቀጣይ የወረዳ ምርጫ ስለሚደረግ ተሸንፈን ስልጣን እንነጠቃለን በሚል ስጋት ብቻ የማሰርና የማሳደድ ዘመቻ ፈጥረዋል።
ይሄ ድርጊት ውሎ ካደረ በኋላ እንደ 2013 አይነት ችግር ተፈጥሮ ለብዙ ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት እንደይሆን ከድርጊታቸው ቢቆጠቡ የተሻለ ይሆናል።
በ2013 አባላትን የማሳደድና የማሰር ዘመቻ ተፈጥሮ ነው ለሁለት ዓመታት የጸጥታ ችግር ዘልቆ የነበረው” ሲሉ አስታውሰው፣ “የአሁኑ ጉዳይም መፍትሄ በቶሎ እንድያገኝ ለክልል ጸጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽንም መረጃ ሰጥተናል፤ እስከሁን ግን አልተፈቱም ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
“ ወረዳ ላይ ካሉ ስምንት አመራሮች አምስቱ ታስረዋል፤ ሦስቱም እየተፈለጉ ነው ”
Date:
