“የሕወሓት እና የሻዕቢያ ጋብቻ በትግራይ ወጣቶች ላይ የታወጀ ሌላ የሞት ፍርድ” ወይዘሮ አረጋሽ አዳነ

Date:

የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ ወይዘሮ አረጋሽ አዳነ፣ አሁን ላይ በሕወሓት ቡድን እና በሻዕቢያ መካከል እየታየ ያለው ትስስር ዋና ዓላማው የትግራይን ወጣት ለተጨማሪ እልቂት መዳረግ መሆኑን ገለጹ።

ሻዕቢያ የራሱን ሕዝብ ችግር መፍታት ያልቻለና በሁከት የሚኖር ድርጅት መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ አረጋሽ፣ አሁን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ለትግራይ ሕዝብ ተቆርቁሮ ሳይሆን የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ እንደሆነ አስረድተዋል።

ሻዕቢያ ቀደም ሲል በትግራይ ውስጥ ንጹሐንን መጨፍጨፉንና ንብረት መዝረፉን ያስታወሱት የቀድሞዋ ታጋይ፣ አሁንም ጦርነቱ ትግራይ ውስጥ እንዲሆንና ከባለፈው እልቂት የተረፈውን የትግራይ ወጣት ለመጨረስ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ኃይል ጋር አብሮ መሥራት የትግራይን ሕዝብ መካድ ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝቡን ዳግም ለከፋ ሰብአዊ መከራና ለባዕዳን ፍላጎት መገበር እንደሆነም በጽኑ አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የሕወሓት ቡድን የሕዝብን ችግር ወደ ጎን በመተው የራሱን የሥልጣን ፍላጎት ለማርካት ከሻዕቢያ ጋር ማበሩን የትግራይ ሕዝብ ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከጥፋት ኃይሎች ጋር መተባበር በሀገርና በሕዝብ ላይ እንደመሰለፍ የሚቆጠር ወንጀል መሆኑን በመግለጽ፣ የትግራይ ወጣት ለዚህ ከንቱ የፖለቲካ ቁማር መሣሪያ እንዳይሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...