የመውጫ ፈተና ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ይፋ ተደረገ

Date:

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች፣ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ተፈታኞች በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው ውጤት ባዩበት https://result.ethernet.edu.et/usernamepage ሊንክ በመግባት “Submit Complaint” የሚለውን አማራጭ በመጫን በኦንላይን ብቻ ማመልከት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፣ የቅሬታ መቀበያ ጊዜው ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚቆይ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ቀላል ማይባል ተፈታኞች እስካሁን ድረስ ውጤታቸውን መመልከት እንዳልቻሉና ለማየት ሲሞክሩ “Pending” የሚል መልዕክት ብቻ እየመጣባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

” ውጤት አላየንም እስካሁን ፤ እሱ ሳይፈታልን ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜው ተገልጿል። ውጤታችንን እንድንናይ ይደረግልን ፤ ችግር ካለም ይፋዊ ማብራሪያ ይሰጠን ” ሲሉ  ተማሪዎቹ ጠይቀዋል።

ከተፈታኞቹ እየቀረበ ስላለው ” Pending ” የማለትና ውጤት አለመታየት ችግርን በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ሚመለከተው ክፍል የስልክ ጥሪ ብናደርግም ለጊዜው ምላሽ ለማግኘት አልቻልንም። ማብራሪያው እንደተሰጠን የምናቀርብ ይሆናል።

tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...