“ካላነበበ ሰው ጋር መወያየትና መግባባት አይቻልም”

Date:

ከአለማየሁ ዋሴ


አቶ ህሩይ ደመላሽ ይባላሉ፡፡ የባሕርዳር ከተማ የረጅም ጊዜ ኗሪ ሲሆኑ አንድ ቀን በቤታቸው ያደራጁትን ቤተ መጽሕፍት እንደጎበኝላቸው በጠየቁኝ መሠረት ግብዣቸውን አክብሬ ቤታቸው ተገኘሁ፡፡


ከዚያ በፊት በአካል የማንተዋወቅ ቢሆንም ቤታቸው ተገኝቼ የግል ቤተመጻህፍታቸውን ሳይ ግን ለረጅም ጊዜ የማውቃቸው ያኽል ተሰማኝ፡፡ በጡሬታ ደመወዝ ውድ ዋጋ ያለቸውን መጽሓፍት ገዝቶ አንድ ክፍል መድቦ ዕውቀትን ፍለጋ ጊዜን ማሳለፍ ምንኛ ትልቅነት ነው፡፡ “ካላነበበ ሰው ጋር መወያየትና መጨዋወት አይቻልም” ይላሉ አቶ ህሩይ፡፡


መጻሕፍትን ከመሰብሰባቸውና ከማንበባቸው በላይ ሶስት ነገሮች በእጅጉ አስደነቁኝ፡-

  1. የሰበሰቧቸው መጻሕፍት ብዛት 2513 ሲሆኑ በይዘት ሳይንስ፣ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ልቦለድ፣ ባዮግረፊ፣ ሀይማኖት (ክርስትናና እስልምና) ያካተቱ ዘርፈ ብዙ መሆናቸው ነው፡፡
  2. አቶ ህሩይ ሲያነቡ ማስታወሻ ይይዛሉ፡፡ ስሜታቸውን የገዛውን አንቀጽ ምዕራፍና ገጹን መዝገበው ማስታዎሻቸው ላይ ያሰፍራሉ፡፡ እናም ማስታዎሻዎቻቸው በራሳቸው ሌላ መጻሕህፍት ሆነዋል፡፡
  3. መጻሕፍቱን ራሳቸው ካነበቡ በኋላ ሌሎች ሰዎች እንዲያነቧቸው ይጋብዛሉ፣ መዝገበው ያውሳሉ፡፡ መዝገባቸው እንደሚያመለክተው እስካሁን ድረስ 526 ጊዜ ለሰዎች አውሰው አስነብበዋል፡፡

አንድ አገሩን አገልግሎ በጡሬታ የተገለለ ሰው ከዚህ በላይና በተሻለ ሁኔታ በሌላ በምን ሊያሳልፍ ይችላል? ፡፡ የኋላ ዘመንን እውቀትንና ልምድን እያጣጣሙና ለሌሎች እየካፈሉ መኖር የአንድ መልካም ዜጋ (Decent Citizen) ተግባር ይመስለኛል፡፡

አቶ ህሩይ ብዙዎች ያለተከተሉትን መልካም የጡሬታ ዘመን ተከትለዋልና አድናቆቴ ይድረሰዎት፡፡ ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ተመኘሁለዎት!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...