የሙላቱ ስንብትና የመክሊት አዲስ አልበም

Date:

የኢትዮ ጃዝ ሙዚቀኛው ሙላቱ አስታጥቄ የስንብት አልበሙን ለአድማጮቹ እነሆ ብሏል። የሙላቱ የወትሮ አድማጮች በመላው አለም ያሉ የጃዝ ወዳጆች እንደመሆናቸው የሙላቱ አልበም መውጣትም ከሀገሩ ይልቅ በባህር ማዶ ሁነኛ ማድመቂያ ሆኖ ሰንብቷል። 

“ሙላቱ ፕሌይስ ሙላቱ” የአልበሙ መጠሪያ ነው። ይህ አልበም ለ81 አመት ባለፀጋው ሙላቱ አስታጥቄ የመጨረሻው አልበሙ እንደሆነ የቅርብ ወዳጆቹ እየተናገሩ ነው።

በእንግሊዝ የአልበሙ ይፋ መደረግን ተከትሎ በነበረ ዝግጅት ላይም የሙላቱ የረጅም ዘመን የሙዚቃ ስኬትን ወዳጆቹና የጃዝ ቤተሰቦች በስስትና በኩራት አክብረውታል። 

አዲሱ አልበም ሙላቱ በህይወት ዘመኑ ከሰራቸውን ሙዚቃዎች የተመረጡ አስራ አንድ ሙዚቃዎችን አሻሽሎና አዳምቆ ያቀረበበት ነው። ሙላቱ አዘውትሮ በሚጎበኘውና ብዙ ታዳሚዎች ባፈራበት በለንደን የረጅም ዓመታት የሙዚቃ ጉዞውን ያከበረ የስንብት ትርዒት አቅርቧል። ትርዒቱ የአዲሱን አልበሙን መውጣት ተከትሎም የተደረገ ነው። 

መክሊት ሀደሮ በጨቅላ ዕድሜዋ ወደየሙላቱ ስንብትና የመክሊት አዲስ አልበም ሀገረ አሜሪካ በስደት የወጣች ድምፃዊት ናት። የመጣችው በርከት ያለ ኢትዮጵያዊ ወደ ሚኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ የነበረ ቢሆንም ቤተሰቦቿ ገጠራማ ወደሆነው አይዋ ግዛት ሄደው ለመኖር ተገደዱ። 

ባደገችበት ከተማ ለአውቶቡስ ተሳፋሪዎች ሳይቀር ካልዘፈንኩላችሁ ትል የነበረችው መክሊት በማለዳው የሙዚቃ ተሰጥዖዋን ገፍታበት አለማቀፍ ዕውቅና የተቸራት ድምፃዊና የሙዚቃ ሃያሲ ለመሆን በቅታለች።

በአሜሪካ ሚዲያዎች አዝውትራ የምትቀርበው መክሊት ከሶስት መቶ በላይ ጣቢያዎችን ባቀፈው በብሄራዊው የራዲዮ ጣቢያዎች ትስስር  NPR የሙዚቃ ጉዳዮች ዘጋቢ በመሆንም ፕሮግራሞችን ታቀርባለች። 

አዲሱ የሙዚቃ አልበሟ “A Piece of Infinity” ከቀደሙት ሙዚቃዎቿ በተለየ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ማንነቶችን የሚያስተዋውቅ ነው። ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ አማርኛን ጨምሮ በአራት ቋንቋዎች አዲሱን አልበሟን ተጫውታለች።

ከተለያዩ የሀገሪቱ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ስልቶችና ዜማዎች በጃዝና በሌሎች ቅንብሮች ተዋዝተው የቀረቡበትም ነው። 

እንደሙላቱ ሁሉ የመክሊትም ሙዚቃ በአብላጫው ኢትዮጵያዊ ባልሆነው አድማጭ ዘንድ የበለጠ የሚደመጡ፣ ሽልማትና ክብር ይዘው የሚመጡ ይመስላሉ። [ዋዜማ]

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...