የስንብት ሥነ ስርዓት

Date:

በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት እና በበርካታ የአደባባይ ምሁራዊ አስተዋጿቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ሻርጃ ከተማ በሚገኘው በአፍሪካ ኢንስቲትዩት ግሎባል ስተዲስ ዮኒቨርሲቲ በፕሮፌሠርነት እና ዲፓርትመንት ሀላፊነት እያገለገሉ ሳለ በአደረባቸው ህመም እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓም ህይወታቸው ማለፋ ይታወቃል።

የፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ የቀብር ሥነ ስርዓት አርብ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይከናወናል።

በዚሁ ዕለት ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ባገለገሉበት የአዲስ አባባ ዮኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ራስ መኮንን አዳራሽ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ የስንብት ሥነ ስርዓት ይካሄዳል።

ዝግጅቱ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ አጋሮቻቸው እና ለአድናቂዎቻቸው ክፍት በመሆኑ በዕለቱ በስንብት ፕሮግራሙ ላይ መገኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...