የሸገሩ ስንክሳር ፕሮግራም መጽሐፍ ሆነ

Date:

በጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ የተዘጋጀውና በርካታ ጉዳዮች የተካተቱበት “እነሆ ስንክሳር” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬድዮ ለዓመታት ሲተላለፈ የቆየው “ስንክሳር” የሬድዮ ፕሮግራም አሁን በመጽሐፍ መልክ እንደተዘጋጀም ተነግሯል።

“እነሆ ስንክሳር”መጽሐፍ የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃም ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ያገኘው መረጀ ያመለክታል።

መጽሐፉ በጃፋር እና በዕውቀት በር መጻሕፍት መደብሮች በኩል ለአንባቢያን ይከፋፈላም ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ላይ በሚያቀርባቸው የስንክሳር፣  የማሟሻ፣ የሃኪሞ መልዕክት፣ የአርብ ምሽት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች እና በኢንቢሲ ቴሌቪዥን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምናውቀው ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ “እነሆ ማሟሻ” የተሰኘ የመጀመሪያ ቅጽ አንድ እና ተከታዩን ቅጽ ሁለት መጻህፍትን በተከታታይ ከዚህ ቀደም ለአንባቢያን ማድረሱ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...