የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር ምርጫ 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የምክር ቤት አባሉን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
ግለሰቡ በስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም፣ በሙስና፣ በቀጥታ በኮንትሮባንድ ዝውውር ውስጥ መሳተፍ፣ ለኮንትሮባንድ አዟዟሪዎች በጥቅም ትሰስር ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና አደንዛዥ ዕጽ በማዘዋወር እንቅስቃሴ ውሰጥ መገኘቱን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ለምክር ቤቱ በዝርዝር አቅርቧል።
የምክር ቤት አባላት በግለሰቡ ዙሪያ የቀረበውን ዝርዝር መረጃ ካደመጡ በኋላ፤ ሌሎች ከግለሰቡ ጋር በጥቅም ትስስር የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው አካላት ላይ በጥልቀት ፍተሻ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።
ግለሰቡ ስልጣኑን መከታ በማድረግ የፈፀማቸው ነገር ግን በወንጀል ሪፖርቱ ውስጥ ያልተካተቱ በርካታ ኢ-ፍትሀዊ ድርጊቶች መኖራቸውን በምክር ቤት አባላቱ ተነሰቷል።
ምክር ቤቱ የግለሰቡ ያለመከሰስ መብትን ለማንሳት የቀረበለትን አጀንዳ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
ምክር ቤቱ በሌላ በኩል የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ስያሜ “አፊኒ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን” እንዲሆን የቀረበለትን አዋጅ መርምሮ ውድቅ በማድረግ የሚዲያ ተቋሙ ቀድሞ ይጠራበት በነበረው ስያሜ “የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን” ሆኖ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳልፏል።
በሚካኤል ገዙ
