232 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን በህንድ ተከሰከሰ

Date:

232 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደለንደን ያመራ የነበረ የኤር ኢንዲያ ንብረት የሆነው ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ከተነሳ በኋላ መከስከሱ ተሰማ።

አውሮፕላኑ ከአህመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳበት ቅፅበት መከስከሱን ቢቢሲ አስነብቧል።

በወቅቱ 12 የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ጨምሮ 232 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን፥ ከተነሳ በኋላ በ190 ሜትር ከፍታ ላይ ከአየር በረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የመጨረሻ ግንኙነት አድርጓል ተብሏል።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን ያልተገለጸ ሲሆን፥ አውሮፕላኑ በመኖሪያ መንደር አካባቢ መከስከሱንም ነው ዘገባው ያመላከተው።

በህይወት ሰው ስለመትረፉ ምንም የተባለ ነገር የለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...