የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወላይታ ዞን፣ በበሌ አዋሳ ከተማ ግዙፍ የቱሪስት ሎጅ ለመገንባት በይፋ አስጀምረዋል።
ይህ ፕሮጀክት በ”ኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን” አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን፣ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ደረጃ ግዙፍ ከሚባሉት የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ እንደሚሆን ተገልጿል።
አቶ ኃይለማርያም በቦታው የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት፣ ሎጁ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን አስታውቀዋል።
ይህ ሎጅ በቴክኖሎጂ እገዛ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ሲሆን፣ ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ወጣቶች በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ታውቋል።
