“የባሕር በር ካለህ ዓለም ሁሉ ገበያህ ነው”

Date:

የኢኮኖሚ ጫና ያለባቸው ሀገራት የባሕር በር አማራጭ ከሌላቸው በልማት ማነቆዎች የተጠፈነጉ እንደሚሆኑ የምጣኔ ሀብት እና የሕዝብ ፖሊሲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፖል ኮሊየር ይገልፃሉ።

“የባሕር በር ካለ ዓለም ሁሉ ገበያህ ነው፤ ከሌለ ግን ከጥቂቶች ጋር ብቻ ትገበያያለህ” በማለት ሃሳባቸውን ያስቀምጣሉ፤ ይህንኑ ሃሳብም በርካቶች ይስማሙበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በቀይ ባሕር ዙሪያ ያሉ የጎረቤት ሀገራትን ሉዓላዊነት እናከብራለን፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀገር ሆና እንድትቀጥል የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት እነርሱም ሊያምኑ እና ሊያከብሩ ይገባል” ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

በታሪክ ብሎም በሕግ የባሕር በር አማራጭ የማግኘት መብት ያላት ኢትዮጵያ፣ ቀይ ባሕርን የማስተዳደር ተሳታፊነት ላይ ልትካተት ይገባል የሚሉት የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ አበራ ሃኢብሳ ናቸው።

ተመራማሪው ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ያለው መረጋጋት እና ሰላም ዘላቂ እንዲሆን በማድረግ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያ የባሕር በር አማራጭ እንድታገኝ መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላትን ሀገር ቆልፎ ማቆየት አግባብ እንዳልሆነ በመግለፅ፤ ይህንንም ለማስቀረት የትውልዱን ጥያቄ ማስመለስ ይገባል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

የፖለቲካ ተመራማሪው አስራት ኤርሜሎ በበኩላቸው፤ በኢኮኖሚ ለመጠንከር ማምረት ብቻ ሳይሆን የተመረተውን ወደ ወጪ የገበያ ንግድ የሚቀርብበት አማራጭ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

አክለውም ሉዓላዊነትን በማጎልበት በባሕር በር ጉዳይ መነጋገርና እና ተጠቃሚነትን ማሳደግ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው ብለዋል፡፡

EBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...