በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ወረርሽኝ 28 ሰዎች መሞታቸውን ተገለፀ

Date:

በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው በኮሌራ ወረርሽኝ እና በወባ በሽታ 28 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአሐዱ አስታውቋል።

‎የትግራይ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር  ዶክተር ሀየሎም፤ በክልሉ በተከሰ የኮሌራ ወረርሽኞች 11 ሰዎች፤ በወባ በሽታ ደግሞ 17 ሰዎች በድምሩ 28 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡

‎በክልሉ ለ3 ወራት የኮሌራ ወረርሽኝ በ18 ወረዳዎች ላይ ተስፋፍቶ እንደነበረና በወረርሽኙ ከተያዙት 556 ሰዎች መካከል 11ቱ ሲሞቱ 545ቱን ሙሉ በሙሉ ማዳን እንደተቻለ አንስተዋል፡፡

‎አሁን ላይ በክልሉ የኮሌራ ወረርሽኝን ሙሉ በሙሉ መቆጣጣ መቻሉን የተናገሩት ዋና ዳይርክተሩ፤ የወባ በሽታ ስርጭቱ ግን የመጨመር መሆኑን አንስተው ከ359 ሺሕ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

‎”በክልሉ የወባ በሽታ መስፋፋቱ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በዘንድሮው ዓመት ከፍተኛ ቁጥር አሳይቷል” ያሉም ሲሆን፤ ከ200 ሺህ ወደ 359 ሺሕ በላይ መመዝገቡን ተናግረዋል።

“‎በክልሉ ከሚገኙ ከሁሉም የጤና ተቋማት መረጃ ለማሰባሰብ የግጭቶችና ጦርነቶች መኖር እንዲሁም፤ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር የምንሰበስበው መረጃ 87 በመቶ ብቻ በመሆኑ ባለው የመረጃ ማሰባሰብ ክፍተት እንጂ ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል” ሲሉም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

‎አሁን ያለንበት ወቅት ክረምት እንደመሆኑ መጠን ሕብረተሰቡ በወባ በሽታ እንዳይጠቃ፤ በየአካባቢው ያቆረ ወሃን በማፍሰስ እራሱን ሊጠብቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...