የታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ብቻ ነው የተሰራው፤ ማንም ምንም ቢል እውነታው አይቀየርም

Date:



ለግድቡ ግንባታ በአጠቃላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ድጋፍ እና ርብርብ ያለምንም የውጭ ዕርዳታ እና ብድር የተገነባ ነው ሲል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በዛሬው ዕለት በተያዘው በጀት ዓመት የተከናወኑና ከሕብረተሰቡ ተሳትፎ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም የጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ፍቅርተ ታዕምር፤ “እኛ ኢትዮጵያዊያን የአባይ ዘመን ትውልዶች 865 የውሃ መጠኑ ከኢትዮጵያ ምንጭ በሆነው አባይ ላይ አሽራችንን ማስቀመጥ ከጀመርን አስራ አራት ዓመታትን አስቆጥረናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አክለውም “የህዳሴ ፕሮጀክትለ እንዴት በሕብረት ጀምረን ማጠናቀቅ እንደምንችል፣ ፕሮጀክት መቅረጽና መምራት፣ ሕዝብን በማስተባበር ለአንድ ዓላማ መቆምን እና ጽናትን ለዓለም ያሳየንበት ነው” ብለዋል።

“ፕሮጀክቱ በፋይናንስ በኩል በመንግሥትና ሕዝብ በራስ ዓቅም ያለምንም የውጭ ዕርዳታም ሆነ ብድር የተገነባ ነው” ያሉም  ሲሆን፤ መላው ኢትዮጵያዊ በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በዕውቀት እና በፐብሊክ ዲፕሎማሲና በአካባቢ ጥበቃ በመረባረብ እዚህ እንዲደርስ ማድረጉን አንስተዋል።

እንዲሁም ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቦንድ ግዢ እና ስጦታ በሀገር ውስጥ 20 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ፣ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ፣ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፤ በአጠቃላይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከህብረተሰቡ ከ23 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ለግድቡ ግንባታ መዋሉን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በመጪው ዓመት ለማስመረቅ ማቀዷን ይፋ ማድረጓን ተከትሎ፤ “ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው” ሲሉ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የግድቡ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ምላሽ የሰጠበት ሲሆን፤ “የታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ብቻ ነው የተሰራው። ማንም ምንም ቢል እውነታው አይቀየርም” ሲሉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...