የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በትላንትናው እለት በዋለው የ50ኛ ዓመት የልደት በዓሌን ምክንያት በማድረግ ከሀገርውስጥና ከውጪ ሀገራት በተለያየ መንገድ መልካም ምኞታችሁን ለገለፃችሁልኝ ወገኖቼ በሙሉ
ላለፉት 25 ዓመታት በሙዚቃ የህይወት ጉዞዬ ውስጥ በስኬቴም በውጣውረዴም ከጎኔ ሳትለዩ እስከዛሬ ድረስ ለሰጣችሁኝ እውነተኛ ወዳጅነት እና ያልተሰሰተ የማያቋርጥ ፍቅራችሁ ፀጋውና በረከቱ ባልተለየኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ::
“ከታላቅ አክብሮት ጋር™
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
