አሜሪካ በኢራን ጦርነት ወደ 37.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ማውጣቷን የመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግዜት ተናገሩ።
ያለፈው ግንቦት ወር ላይ ከቀረበው የ8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የአሁኑ ከፍተኛ ነው።
ሄግዜት ለአሜሪካ ሴኔት በሰጡት ማብራሪያ ለፔንታገን ተጨማሪ 87 ቢሊዮን ዶላር እንዲመደብ ጠይቀዋል። ከዚህ ገንዘብ 67 ቢሊዮን ዶላሩ በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚካሄድ ኦፕሬሽን የሚውል ነው ብለዋል።
ሄግዜት ማብራሪያ በሚሰጡበት ወቅት ጦርነቱን የሚቃወሙ ሰዎች ድምጻቸውን በተደጋጋሚ በማሰማት ንግግራቸውን አቋርጠዋል።
ኢራን እና አሜሪካ በድጋሚ ወደ ግጭት ከተመለሱ ወዲህ ሄግዜት በካፒቶል ሂል ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ሦስት አሜሪካውያን ወታደሮች በኢራን ጥቃት ተገድለዋል።
ዋይት ሀውስ ለቀጣዩ በጀት ዓመት 1.5 ትሪሊዮን ዶላር እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
አሜሪካ በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት 11ኛ ቀኑን ይዟል።
