የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ አዲስ የተኩስ አቁም ሀሳብ አቀረቡ። የተኩስ አቁሙን ሀሳብ ዝርዝር ይፋ ባያደርጉም ትራምፕ እስራኤል ተቀብላዋለች ብለዋል።
ምንም እንኳን ሀሳቡን ቴል አቪቭ ብትቀበለውም ከሃማስ በኩል ያለው ቁርጠኝነት ወሳኝነት እንዳለው ተነግሯል። ሃማስ ከአሜሪካ የተኩስ አቁም ሀሳብ ደርሶኛል ከማለት ያለፈ አቋም አለማንጸባረቁ ግን ተወስቷል።
ትራምፕም የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ ለሃማስ መስጠታቸውን አሳውቀዋል። ሃማስ በግልጽ የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳቡን ካልተቀበለ አደገኛ ውጤት ይኖረዋል ሲሉም ዝተዋል ሪፐብሊካኑ።
ሁለት ዓመት ሊሞላው ሁለት ሳምንታት ገደማ በቀረው የሃማስ እና የእስራኤል ኃይሎች ጦርነት ቴል አቪቭ በተደጋጋሚ የዋሽንግተንን የተኩስ አቁም ጥሪ ተቀብያለህክ በማለት ብትታወቅም በግልጽ ጋዛን ማሸነፍ አለብኝ ስትል ትደምጣለች።
“ሁሉም ሰው ታጋቾች ወደ ቤት እንዲመለሱ ይፈልጋል።ጦርነቱ እንዲቋጭ የማይፈልግ የለም” ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል ዶናልድ ትራምፕ ።
“ከእንግዲህ ዳግም ለሃማስ ዕድል አልሰጥም ።የመጨረሻ ማስጠንቀቂያም ነው ብለዋል ።
የጋዛው ሃማስ ከአሜሪካ የተኩስ አቁም ጥሪ ሀሳብ መቅረቡን አረጋግጦ ለውይይት በጠረጴዛ ዙሪያ ለመቀመጥ ዝግጁ ነኝ የሚል ምላሽ ሰቷል።
ይህ ማለት ግን እስራኤል ተቀበለችው የተባለውን የትራምፕ ተኩስ አቁም ሀሳብ ሃማስ ተቀብሎታል ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው። NBC Ethiopia
