የትግራይ ሰላም ሀይል(ቲፒኤፍ) መግለጫ አወጣ

Date:

መግለጫውም‹‹ሰላም ምርጫችን ነው፣ ፍትህ ተልእኳችን ነው፣ አንድነት ግባችን ነው›› በሚል የጀመረው ቲፒኤፍ ሲቀጥልም በትግራይ ሰላም፣ ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከአመፅ ይልቅ እርቀ ሰላምንና ሰላማዊ መፍትሄዎችን ለማምጣት በሚል እንደሚንቀሳቀስ ገልፆም ጦርነትን አማራጭ አድርጎ እንዳልተመሰረተ አስታውቋል፡፡ ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ በሰናሌ የሚንቀሳቀሱ ወታደራዊ ሀይሎች እያደረሱበት ያለውን ግጭት ቀስቃሽ ሁኔታዎች ተከትሎ ሌላ አማራጭ መንገድ ለመከተል መገደዱን አስረድቷል፡፡

‹‹ግጭቱን እኛ አልጀመርንም፣ ትርጉም አልባ ወደሆነው ውስጣዊ ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎትም የለንም›› ያለው ቲፒኤፍ በኢስራ አዲ፣ ዋጅራትና አካባቢው ለተፈፀመበት ጥቃት ተመጣጣኝ መልስ መስጠቱን ገልጿል፡፡ ይህም ሰላም የመጀመሪያና ብቸኛው አማራጭ ነው ከሚል አላማው በመነሳት ያደረገው መሆኑን ጠቅሶ ‹‹ፖለቲካዊ አድልኦንና ወታደራዊ ተቋማነትን ለፖለቲካዊ ጥቅም ማዋልን›› እንደሚቃወም አስረድቷል፡፡

ሲቀጥምል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ማለትም ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሁሉንም የትግራይ ዞኖች ድምፅና ፍላጎት የሚያንፀባርቅና የሚወክል የክልል ካቢኑ በአስቸኳይ እንዲያቋቁሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ‹‹እውነተኛ መረጋጋት በክልላችን ሊመለስ የሚችለው በፍትሀዊ አስተዳደርና በዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ብቻ ነው›› ያለው ቲፒኤፍ ተልእኮውም ዘላቂ ሰላም ማስፈንና አምባገነንነትን መመከት መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ይሁንና አንዳንድ ‹‹አደመ ህወሀት›› ያላቸው አካላትና ወታደራዊ አዛዦች ማስፈራራታቸውንና የሀይል እርምጃ ለመውሰድ መዛታቸውን እንደቀጠሉበት አስረድቷል፡፡

ቲፒኤፍ በዚህ መግለጫው ለትግራይ መከላከያ ሀይል(ቲዲኤፍ) አባላትም መልእክት አስተላልፏል፡፡ በመልእክቱ ‹‹በቲዲኤፍ ውስጥ ያላችሁ ወንድምና እህቶቻችን አሁን በጋራ ትግላችን እጣ ፈንታ ላይ በጥልቀት የምናሰላስልበት ጊዜ ነው፡፡ ቀጣይ መንገዳችን የአንድነት፣ ዲሞክራሲያዊ ተሀድሶና በሰላም አብረን የምንኖርበት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም ከጦርነት ኢኮኖሚና ከአምባገነናዊ አስተሳሰብ ተላቃችሁ ከህዝብ ጎን እንድትሰለፉ እናሳስባለን›› ማለቱን ትግራይ ሄራልድ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...