የኃይል ሥርቆት የፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ

Date:



የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና ክትትል ማግኘቱን አስታውቋል።

ሪጅኑ በ196 ሺሕ ደንበኞች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል 13 በስማርት ቆጣሪዎች፣ 69 በቅድመ ነጠላና ባለሦስት ፌዝ ቆጣሪዎች እና በ29 የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ላይ ስርቆቱ መፈፀሙን  የሸገር ሪጅን ኢነርጂ ማኔጅመንት ማናጀር አቶ ግርማ ተናግረዋል።

ዘመናዊ ቆጣሪዎች (ስማርት ) ላይ የተደረገው ስርቆት የታወቀው ቆጣሪዎቹ ወደ መረጃ ቋት በሚልኩት መረጃ ነው።የኃይል ስርቆት በፈፀሙ ደንበኞች ላይ ከ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ እንዲከፍሉ በማድረግ ሊባክን የነበረ ከ17 ሚሊየን በላይ ኪዋት ሰዓት ከብክነት ታድገናል ሲሉ ማናጀሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የኃይል ስርቆት ሲፈጽሙ በተገኙ  ደንበኞች ላይ ክስ መመስረቱ ተገልጿል።የኃይል ስርቆት ተግባር ሲፈፅም የተገኘ አካል በሕግ ከመጠየቁም ባለፈ፣ ይጠቀምበት የነበረው አገልግሎት እንደሚቋረጥ፣ ያለአግባብ ለተጠቀመው የፍጆታ ሂሳብ በታሪፉ መሰረት ተሰልቶ ከዳግም ማስቀጠያ ክፍያና ከተጨማሪ ቅጣት ጋር እንዲከፈል  ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም የኃይል ስርቆት መፈፀም በወንጀል የሚያስከስ እና እስከ አምስት ዓመት በእስራት የሚያስቀጣ እንዲሁም እስከ 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ነው ሲሉ አቶ ግርማ ወግበላ ጨምረው መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ዘግቧል።
@ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...