የኔቶ ተዋጊ ጀቶች  ከሩሲያ ሀይሎች ጋር ፍጥጫ

Date:


የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት የሩሲያ ኑክሌር አቅም ያላቸው ቦምብ ጣዮች በፈጠሩበት ስጋት ምክንያት የጦር ጀቶቹን አሰማራ።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቲዩ-22M23  ረዥም ርቀት  ቦምብ ጣዮች በኤስዩ-57 ጀቶች ታጅበው ለአራት ሰዓታት በዓለም አቀፉ የውሃ አካል ላይ ተልዕኳቸውን ፈፅመዋል የሚል መረጃ አጋርቷል።

በባልቲክ ባህር ላይ የነበረውን እንቅስቃሴ ለመግታት ኔቶ ጀቶቹን አሰማርቶ ስጋቱን ለመቀነስ ሞክሯል ተብሏል።

በኔቶና ሩሲያ መካከል በዚህ ቀጠና ላይ ከባድ ወታደራዊ ውጥረት ተፈጥሯል።

የጥምረቱ ጀቶች የሩሲያን ሀይሎች እንቅስቃሴ መለየት መቻላቸውንም ዘገባዎቸወ ይጠቁማሉ።

ሞስኮ በረራዎቹ በዓለም አቀፍ የአየር ክልል አጠቃቀም ህግ መሰረት ያደረገችው በረራ ነው ብትልም ኔቶ ስጋት ለመፍጠር የተደረገ ዘመቻ ነው በሚል ይወቅሳል።

ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶች በኔቶ በኩል ጥቅም ላይ ውለዋል።

ሩሲያ ባልቲኮቹ (ኢስቶኒያ፣ላቲቪያ እና ሉትዌኒያ) እንዲሁም ፊንላንድ ለዩክሬን ሀይሎች አየር ክልላቸውን አሳልፈው እየሰጡ ነው በሚል መክሰሷ አይዘነጋም።

በባልቲጅ አካባቢ ያለውን ሀብት ለመቆጣጠር ኔቶ የራሱን ክልል እየፈጠረ ነው በሚልም ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቱን ይወቅሳሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...

በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን...