Home ልዩ ልዩ ዜና የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ መሻሻያ ሊደረግለት ነው

የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ መሻሻያ ሊደረግለት ነው

የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ መሻሻያ ሊደረግለት ነው

በሸማቾች ላይ የሚፈፀምን የመብት ጥሰት ምላሽ ይሰጣል የተባለ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ መሻሻያ ሊደረግለት መሆኑ ተገልጿል።

ይህን ያሉት በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሸማች መብት ጥበቃና የግንዛቤ ፈጠራ ዴክስ ሃላፊ አቶ ሰይፉ አየለ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

አቶ ሰይፉ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ የሸማቾችን መብት ከመጠበቅ አንፃር መደረግ የሌለባቸውንና ያለባቸውን ተግባራት በመዘርዘር አስቀምጧል ነው ያሉት።

ይሁንእና ማሻሻያ ያልተደረገለት አዋጁ የመብት ጥሰት በሸማቹ ላይ ሲደርስ፣አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ሲኖር ፣ በምርቶች ላይ አግባብነት የሌለው ባእድ ነገር ሲያጋጥም ሸማቹ መብቱን ለማስከበር የሚያልፍበት ሂደት አሰልቺ እንደሆነ አንስተዋል።

ይህን ችግር ለመፍታት አዋጁን በማሻሻል በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚኛው ማሻሻያ ሸማቹ ወዲያውኑ ብዙ ሳይደክም ምላሽ የሚያገኝበትን አሰራር መዘርጋቱን አንስተዋል።

የንግዱን ህብረተሰብ ከፀረ-ውድድር እና ተገቢ ካልሆኑ የገበያ ተግባራት እንዲሁም ሸማቹን ከሚያሳስቱ የገበያ ሁኔታዎች የሚከላከልና ለነፃ ገበያ ውድድር አመችነት ያለው ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል ፡፡