የንግድ ዘርፉን ለማሳደግ ከውጭ ሀገራት ጋር ቢዝነስ መፍጠር ይገባል

Date:

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) የንግዱን ዘርፍ ወደ ተሻለ ለውጥ ለማሳደግ ከውጭ ሀገራት ጋር የቢዝነስ ትስስርን ለመፍጠር የሚያስችል የኢትዮ-ቤልጂየም የንግድ ኮንፍረንስ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

የምክር ቤቱ ዋና ተጠባባቂ ዋና ጸሐፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ የንግዱን ዘርፍ ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ከቤልጂየምና በሉግዘምበርግ ንግድ ዘርፍ የተወጣጡ አካላት ጋር ተሞክሮዋቸውን ወይንም የልምድ ልውውጥ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት የኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን ሚና እያበረከተ የሚገኝ ተቋም መሆኑን አንስተው፤ ዘርፉን ለማሳደግና ዘርፉን በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“ይህ ሲሆን የህብረተሰቡን መብት ፍላጎትና ጥቅም ለማሳደግ የንግድ ትስስር እንዲፈጠር፣ የውጭ ሀገር ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባና የሀገር ውስጥ ገጽታ እንዲገነባ የሚያስችል አሰራር መፍጠር ይገባል” ብለዋል።

ምክር ቤቱ ይህንን ጉባኤ ሲያዘጋጅ በቤልጂየም ኤምባሲ፣ በሉግዘምበርግ ንግድ ምክር ቤት፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ትብብር ማድረጉን አስታውቀዋል።

በዚህ የቢዝነስ ተልዕኮ ላይ ከቤልጂየም የመጡ በግብርና፣ በታዳሽ ሃይል፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በሕክምና እንዲሁም በፕላስቲክ መልሶ ማልማት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በኢትዮዮጵያ በመገኘት ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን  አስተዋውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ ተመሳሳይ ኩባንያዎች ጋር የቢዝነስ የልምድ ልውውጥና ትስስር የሚፈጥር መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።

የንግድ ኮንፈረንሱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን እና የአዲስ አበባ ቻምበር ተ/ዋና ፀሐፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ መልዕክት አስተላልፈዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...