የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራት የአፍሪካ ሀገራትን ይጎበኛሉ

Date:

የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት ከነገ ጀምሮ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው። ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር “በቀጠናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች” ላይ እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ምክትል ሚኒስትሩ በዚሁ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ግብጽ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ ይጓዛሉ። የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመጋቢት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ክሪስቶፈር ላንዳው፤ ወደ ካይሮ እና አዲስ አበባ የሚጓዙት የሀገራቸው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ እና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት የገቡበትን ውዝግብ ለመፍታት እንደሚሹ ባስታወቁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው።

የላንዳው የመጀመሪያ መዳረሻ በሆነችው ግብጽ፤ ላንዳው “በአካባቢያዊ ተግዳሮቶች” ላይ ስለሚደረግ ትብብር ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ መስሪያ ቤታቸው ገልጿል። በእነዚህ ውይይቶች የአሜሪካ እና የግብጽ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ማጠናከርን የተመለከቱ ጉዳዮች እንደሚነሱም መስሪያ ቤቱ አመልክቷል።

የአሜሪካው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከካይሮ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ፤ በዩናይትድ ስቴትስ ጦር የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን አብረዋቸው ይጓዛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ባለፈው ህዳር በአዲስ አበባ ተገናኝተው እንደነበር ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በዘገባው አስታውሷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...