በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቭን ሆሴ ማሲንጋ ዛሬ ጠዋት ሽሬ ከተማ ገብተዋል፡፡
የአምባሳደሩ ወደ የሽሬ ከተማ ጉብኝት ዓላማ፣ የአሜሪካ መንግስት ለተፈናቃዮች የሚያደርገው የሰብዓዊ ድጋፍ ያለበትን ሁኔታ ለመገምገምና የፕሪቶሪያውን የተኩስ አቁም ሙሉ በሙሉ በሚተገብሩበት ሁኔታ ላይ በመምከር ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ነው ተብሏል፡፡
አምባሳደሩ ሙሉ ቀን በሚወስደው ጉብኝታቸው፣ ከአካባቢው መሪዎች ጋር በመገናኘት በፖለቲካ አካታችነትና በሰላም ዙሪያ እንደሚመክሩም በአሜሪካ ኤምባሲ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባሰፈሩት መረጃ ጠቁመዋል፡፡
ይህን ተከትሎም በርካታ የህወሓት ጄኔራሎች ትናንት ሽሬ ገብተው ማደራቸው ታውቋል፡፡
