የአሜሪካ ኤምባሲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲን በይፋ አመሰገነ

Date:

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በአጼ ቴዎድሮስ ካምፓስ የሚገኘውን ዋና ቤተመጻሕፍት በአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማን ስም በመሰየሙ በይፋ አመስግኗል፡፡

“የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአጼ ቴዎድሮስ ካምፓስ የሚገኘውን ዋና ቤተ መፃህፍት “የትሩማን ቤተ መፃህፍት” ብሎ በመሰየም ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማንን በመዘከሩ እናመሰግናለን።” ብሏል የአሜሪካ ኤምባሲ፡፡

ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው የምስጋና ቃል፤ “ይህ ክብር እ.ኤ.አ በ1954 የጎንደር የማህበረሰብ ጤና ኮሌጅና የማሰልጠኛ ማዕከልን (የአሁኑ ታዋቂው የጎንደር ዩኒቨርሲቲን) ለመመስረት የረዳውን የፖይንት ፎር ዓለማቀፍ የትብብር መርሃ ግብር በማስጀመር ረገድ ፕሬዚዳንት ትሩማን ለተጫወቱት ወሳኝ ሚና እውቅና የሚሰጥ ነው” ብሏል፡፡

ዕውቅናው የዩኒቨርሲቲው 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት የምስረታ በአል ላይ ይፋ መደረጉን የጠቀሰው ኤምባሲው፤ ይህ ምዕራፍ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል በትምህርት፣ በማሕበረሰብ ጤናና በማህበረሰብ ልማት ያለውን ዘላቂ ትብብር እንደሚያሳይ ጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም፤ “ይህንን የጋራ ታሪክ በመዘከራችን ኩራት ይሰማናል፤ እናም ይህን ተጽዕኖ ፈጣሪ አጋርነት ለመቀጠል በጉጉት እንጠብቃለን!” ብሏል።(አ.አ.ኦ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች”:-  ከዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል ጋራ ውይይት

ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል በተለይ በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ 97...

የ12ኛ ክፍል የፈተና ቀን ታወቀ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሳልቫ ኬር ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት...

አሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው !

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት...